ብቃት ያለው ሰልጣኝ እንዲወጣ ለማድረግ ኮሌጁና ካምፓኒዎች በጋራ በመስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ለኢንዱስትሪ አሰልጣኞች ሲሰጥ የነበረው የማስተማር ስነ ዘዴ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ የተገኙት የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ዮሐንስ ሁንዱማ ኢንደስትሪው እና ኮሌጁ ብቁና በገበያ ተፈላጊ እንዲሁም ተወዳዳሪ ሰልጣኝ ለማፍራት ሀላፊነታችንን በጋራ መወጣት አለብን ብለዋል፡፡
አቶ ዮሐንስ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና ስርዓት በኮሌጅ ብቻ የተገደበ ባለመሆኑ ሰልጣኞች የስራ ላይ ልምምድ ለማድግ ወደ ተቋማችሁ ሲመጡ አስፈላጊውን የተግባር እና የስራ ቦታ ስነ ምግባር በተመለከተ ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ ይጠበቅባችኋል ብለዋል፡፡
ወደ ድርጅታችሁ የስራ ላይ ልምምድ ለማድግ የሚላኩ ሰልጣኞች ለእናንተም ለሀገርም ግብአት የሚሆኑ ናቸው፡፡ ሰልጣኞቹ በስልጠና ላይ እያሉ የናንተ ሰልጣኞች ሲሆኑ ስልጠና አጠናቀው ሲወጡ ደሞ የድርጅታችሁ ተቀጣሪ ስለሚሆኑ ማግኘት ያለባቸው ስልጠና በአግባቡ እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል፡፡
በስልጠናው የተሳተፉ ባለሙያዎች በቀጣይ ወደ ተቋማችሁ ለትብብር ስልጠና ተልከው የሚመጡ ሰልጣኞች ማግኘት ያለባቸውን ስልጠና በአግባቡ እንዲያነኙ እና መሞላት ያለበትን ውጤት በአግባቡ እንዲሞላ እንዲሁም ሰልጣኞች ሰርተው መለወጥ እንደሚችሉ በማሳየት የሙያ ስነ ምግባር እንዲላበሱ ማድረግ እንደሚገባ የኮሌጁ የተቋማት ልማትና አስተደደር ጉዳዮች ም/ዲን ወ/ሮ ዋጋዬ ገ/መድህን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም ኮሌጁ ከኢንዱስትሪው ጋር የተለያዩ ስራዎችን እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በመጨረሻም በስልጠናው ለተሳፉ የኢንደስትሪ ባለሙያዎች የምስክር ወረቀት እና የተባባሪነት እውቅና ተሰቷል፡፡
.