አስደሳች
ዜና ለሥልጠና ፈላጊዎች በሙሉ
ምሥራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በከተማችን ከሚገኙ ስድስት የመንግስት ፖሊ
ቴክኒክ ኮሌጆች መካከል አንዱ ነው፡፡ ኮሌጃችን በገበያ ፍላጎት
መሰረት ክህሎት ያለው፣ በዲሲፕሊን የታነጸ፣ ተነሳሽነት የተላበሰና ከአዳዲስ አሰራሮች ጋር ተዋህዶ ስራውን የሚያከናውን
የሰለጠነ የሰዉ ኋይል ማፍራትን ዓላማ አድርጎ ደረጃውን በጠበቀ
እና በተሟላ የማሰልጠኛ ወርክ ሾፕ ለ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በቀን እና በማታ በቅዳሜና እሁድ መርሃግብር በሚከተሉት
የሙያ ዘርፎች ከደረጃ 1- 5 ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ስለሆነም የስራና ክህሎት ሚ/ር
ያወጣውን የመግቢያ መስፈርት የምታሟሉ መጥታችሁ እንድትመዘገቡ ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡