Announcement የአሰልጣኞች የዝውውርና የምደባ  አፈፃፀም ደንብ  ዙሪያ ለማኔጅመንት አባላት እና ለዲፓርትመንት ተጠሪዎች ስልጠና ተሰጠ።

የአሰልጣኞች የዝውውርና የምደባ  አፈፃፀም ደንብ  ዙሪያ ለማኔጅመንት አባላት እና ለዲፓርትመንት ተጠሪዎች ስልጠና ተሰጠ።

04th September, 2025

የአሰልጣኞች የዝውውርና የምደባ  አፈፃፀም ደንብ  ዙሪያ ለማኔጅመንት አባላት እና ለዲፓርትመንት ተጠሪዎች ስልጠና ተሰጠ።

በምሥራቅ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዞኒንግና ዲፈረንሼሽን ትግበራ  የአሰልጣኞች የዝውውርና የምደባ  አፈፃፀም ደንብ  ዙሪያ  ለማኔጅመንት አባላት እና ለዲፓርትመንት ተጠሪዎች ስልጠና ተሰጠ። 

ምደባው በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የሰልጣኝ አሰልጣኝ እንዲሁም የማሰልጠኛ ክፍሎች ጥምርታን በማጣጣም ኮሌጆች አካባቢያዊ የመልማት ፀጋቸውን መሰረት አድርገው ጥራት ያለው ስልጠና ለመስጠት ታስቦ የሚካሄድ ድልድል እንደሆነ የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ዮሐንስ ሁንዱማ በእለቱ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ገልጸዋል፡፡

የአሰልጣኞች የዝውውርና የምደባ  አፈፃፀም ደንብ ዙሪያ የኮሌጁ የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክሬት አቶ ተካ ያስራሽ ገለፃና ማብራሪያ ተሰቷል።

1.  ምደባ የሚካሄደው በስልጠና ዘርፉ በየ ሙያ መስኩ ያሉ ሰልጣኞችን መሰረት ተደርጎ  የ  "ቢ" ወይም የ"ኤ" አሰልጠኝ ደረጃ ያሟላ አሰልጣኝ ብቻ ይሆናል፡፡

2.  በተቋሙ የተፈቅዶለት ትምህርት ላይ የሚገኝ ወይም ከሶስት ወራት በላይ በስልጠና ላይ የሚገኝ አሰልጣኝ በዚህ ውድድር ላይ አይካተትም 

3.  በሰው ሀብት አስተዳደር መመሪያ መሰረት ተቋሙ ፈቅዶና እውቅና በሰጣቸው ምክንያቶች እንደ ወሊድ የአመት ፍቃድ ያለ ደሞዝ ፍቃድ እስከ ሶስት ወራት ያሉ አጫጭር ስለልጠና ላይ የሚገኙ ወይም የህመም ፍቃድ በድልድል ወቅት በስራ ላይ ያልተገኘ አሰልጣኝ በሰው ሀብት አስተዳደር ዳሬክቶሬት መረጃ አቅራቢነት እንዲያቀርብ ይደረጋል፡፡

4.  ውድድር የሚደረገው በዞኒንግ እና ዲፈረንሴሽን ጥናት መሰረት በቢሮው በተፈቀዱ የስልጠና ዘርፎች ላይ ብቻ ይሆናል

5.  በተፈቀዱት የሙያ ዘርፎች የሚወዳደሩት አሰልጣኞች ቀደም ብሎ በስልጠና ዘርፍ ላይ ተመድበው ሲያሰለጥኑ የነበሩ አሰልጣኞች ብቻ ይሆናሉ በሌላ የስልጠና ዘርፍ ላይ ያለ አሰልጣኝ መወዳደር አይችልም

6.  በኮንትራት ወይም በጊዜአዊነት ተቀጥረው የሚያገለግሉ አሰልጣኞችን በምደባ ማሳተፍ አይቻልም

7.  በዞኒንግ እና ዲፈረንሴሽን ጥናት መሰረት በተዘጉ ወይም በማይቀጥሉ የስልጠና ዘርፎች ወይም ክፍሎች ድልድል አይደረግም

8.  በተዘጉ ወይም በማይቀጥሉ የሙያ ዘርፎች ላይ ተመድበው ሲሰሩ የነበሩ አሰልጣኞች በመስፈርቱ መሰረት ውጤታቸው ተሞልቶ በተቋሙ የበላይ ሀላፊ ተፈርሞ ዝርዝራቸው ለቢሮ የሚላክ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

የመመዘኛ መስፈርት

1.  የትምህርት ዝግጅት

2.  አማካኝ መመረቂያ ውጤት

3.  አካዳሚክ ማእረግ

4.  የሙያ ብቃት ውጤት

5.  የስራ አፈጻጸም ምዘና

6.  በዘርፉ የሚሞላ ውጤት

መሰረት አድርገው የሚካሄድ እንደሆነም አቶ ተካ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ለኮሌጁ አጠቃላይ ለአሰልጣኞች ገለጻ የሚደረግ እንደሆነ እና ከዞኒንግ ውጪ ያሉ ሙያዎች ሲያሰለጥኑ የነበሩ እና በኮሌጁ ምደባ ያላገኙ አሰልጣኝ በተለያዩ ኮሌጆች እና ሴክተር ተቋማት እንደሚመደቡ  የኮሌጁ ዋና ዲን ገልጸዋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with