Announcement ምሥራቅ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ፖሊሲ

ምሥራቅ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ፖሊሲ

16 Jul 2025

ኮሌጅ ከፍተኛ ጥራት ያለው የቴክኒክናሙያ ስልጠናን ከስራ ፈጠራ እንዲሁም ከፈጠራ ችሎታ ጋር በመስጠት ለገበያው ብቁፈጣሪና ተነሳሽነት ያላቸው ተመራቂዎችን በማፍራት ረገድ የልህቀት ማዕከል ለመሆን ቁርጠኛ ነው፡፡ከዚህም በተጨማሪ ኮሌጁ ምርታማነትን የሚያጎለብቱናዘላቂ ሀብት የሚፈጥሩ አስፈላጊ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር፣ በማሸጋገር እንዲሁም በክፍተት ላይ ያተኮረ የኢንዱስትሪ ድጋፍ አገልግሎቶችንበመስጠት ሰልጣኞችና ሌሎች ተጠቃሚዎችንለማርካት ይሰራል።

ምስራቅ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በISO 21001:2018 ላይ የተመሠረተ የትምህርት ተቋም አስተዳደር ስርአት በመተግበር፣ በመከታተል፣ በመቆጣጠር፣ በመገምገምናበማስቀጠል እንዲሁም ሌሎች ተፈፃሚነት ያላቸውን ደንቦችናየህግ ማዕቀፎችተግባራዊ በማድረግ የሰልጣኞችንናየሌሎች ተጠቃሚዎችን ፍላጎት ለመለየት፣ ለማሟላትና በየጊዜው ክትትል ለማድረግ የማያቋረጥና ቀጣይነት ያለው ጥረት ያደርጋል፡፡በተጨማሪምዘላቂ የአሰራር ልምዶችን በመከተል፣ አካታችነትን በማጎልበት፣ ማህበረሰባዊ ችግሮችን በመፍታትና በአካባቢ ላይ የሚደርሰውን ተፅዕኖበመቀነስ የማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ቁርጠኛ ነው።

አዳዲስየትምህርት፣ የሳይንስና እና የረቀቁ ቴክኖሎጂ ግኝቶችን/ውጤቶችን መከታተል፣ መለየትና መጠቀም፣  አዕምሮአዊ ንብረትን በኃላፊነት ማስተዳደር፣ የተራቀቁ ቴክኖሎጂዎችንመጠቀም፣ቀጣይነትባለው ስልጠና የሠራተኞቻችን አቅም ማሳደግ፣ የአገልግሎት ጥራትን ማሻሻል፣ የኢንዱስትሪ መስፈርቶችን ማሟላት፣እንዲሁም ህጋዊነትያለው አፈጻጸምንማረጋገጥ ለተወዳዳሪነትና ለስኬታማነት ወሳኝ መሆናቸውን ያምናል።

የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮች በቂ ሀብት በመመደብ፣የደንበኞችንአስተያየት በመሰብሰብ፣ የማስተካከያና የቅድመ መከላከል አሰራሮችን በመተግበር እንዲሁም የትምህርት ተቋም አመራር ስርዓቱ በሚያልፍበትሂደት ውስጥ ብቁየሆነ፣ ውጤታማና የማያቋርጥ መሻሻል እንዲያሳይ ትልቁን ሃላፊነት ይወስዳል። በተጨማሪምከፍተኛ አመራሩ ሁሉም የኮሌጁ ሠራተኞች በራሳቸው የሥራመስክ ያሉባቸውን ኃላፊነቶች በመረዳት የትምህርትአስተዳደር ስርዓቱን ከሁሉም የስራ ደረጃዎች ጋር በማጣጣም በሚቀር ሪፖርቶችና ግልፅ የሆኑ የሐሳብ ልውውጦች ውስጥ ስርአቱንማካተታቸውን የማረጋገጥ ሀላፊነት አለበት።

Copyright © All rights reserved.

Created with