የፕረስ መግለጫ
ከምሥራቅፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ምሥራቅ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ11 ዲፓርትመንትበተለያዩ ሙያዎች ያሰለጠናቸውን 850 ሰልጣኞች የምርቃትስነ- ስነስርዓት በነገው እለት በሚሊኒየም አዳራሽ ያካሂዳል፡፡
ኮሌጁ ውጤት ተኮር ስልጠና በመስጠት ውጤታማ፣ በራሱየሚተማመን ፣ ብቁ የፈጠራ ችሎታ ያለው እና በስራ ገበያ ተፈላጊ የሆነ የሰው ሃይል በማፍራትየኢንዱስትሪውን የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎትለማሟላት በለያዩ የሙያ ዘርፎች ሲያሰለጥን መቆየቱ ይታወቃል፡፡
በነገው እለት መስከረም 10/2017 ዓ.ም ከደረጃ ሁለት እስከ ደረጃ አምስት በተለያዩየሙያ ዘርፎች ስልጠናቸውን የተከታተሉ 850 ሰልጣኞችንበሚሊኒየም አዳራሽ ያስመርቃል፡፡
መስከረም 10/2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ በሚያካሂደው የምርቃት ስነ-ስርዓትየአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አበቤ፣ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊክቡር አቶ ጥራቱ በየነ እና ሌሎች የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ የኮሌጁ ዲኖች እና አሰልጣኞች እንደሚገኙ ይጠበቃል፡፡